ታሪካችን

Tent Era

፲፱፻፹፭ - ተመሠረተ

በሂውስተን በምህፃረ ቃል (CMSDSM) በመባል የሚታወቀው የደብረ ሰላም መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በሂውስተን እና በአካባቢዋ ለሚኖሩ ክርስቲያኖች መንፈሳዊ አገልግሎት ለመስጠት ሐምሌ ፳፯ ቀን ፲፱፻፹፭ ዓ.ም. (Aug 4, 1993) የቅዱስ ሲኖዶስ ፈቃድ ተሰጥቶት ተመስርቷል።

Building Construction

፲፱፻፹፱ - ምረቃ

በሂውስተን በፍትነት በማደግ ላይ ያለው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ማህበረሰብ፣ መጀመሪያ በቅዱስ ማርቆስ ግብፅ ቤተክርስቲያን መሰብሰብ የጀመረ ሲሆን፣ በኋላም በ፲፱፻፹፮ ዓ.ም. (December 1993) ፪.፭ ኤከር መሬት ገዝቶ እስከ ነሐሴ ፲፱፻፹፯ ዓ.ም. (August 1995) ድረስ በድንኳን ውስጥ አገልግሎት ሲሰጥ ቆይቷል።

Future Expansion

እድገት እና መስፋፋት

በወቅቱ በምዕራብ ሲል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ የነበሩት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ይስሐቅ የአሁን ህንፃ መሰረት ድንጋይ ጣሉ። ቤተክርስቲያኑም ተገንብቶ ጥቅምት ፴ ቀን ፲፱፻፹፱ ዓ.ም. (November 9, 1996) በወቅቱ በአሜሪካ ነዋሪ በነበሩት በሦስቱም ሊቃነ ጳጳሳት (አቡነ ይስሐቅ፣ አቡነ ዜና ማርቆስ እና አቡነ መልክ ጼዴቅ) ተባርኮ ተመርቋል።

የወደፊት ራዕይ

ይህ ንቁ ማህበረሰብ በሂውስተን እና በአካባቢው እየጨመረ የመጣውን ምእመን ለማስተናገድ እጅግ ትልቅ ህንፃ ለመገንባት ገንዘብ በማሰባሰብ ላይ ይገኛል።

ራዕዩን ይደግፉ